ለሁሉም የከተማዋ ነዋሪ ዜጋ የሚሆን አገልግሎት መስጠት ተቀዳሚ አላማችን ነው፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ እና ክህሎት ቢሮ

        የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የሥራ እና ክህሎት ቢሮ  አዳዲስ የስራ ፈጠዎችን ፤ የኢንተርፕራይዝ መመስረት ፤ የስራ እድገት ማበረታቻ ፤    አዳዲስ ቴክኖሎጊዎችን ማስተዋውቅ እና ከአነስተገኛና ጥቃቅን ወደ ከፍተገኛና ራሳቸውን በራሳቸው ማሰትዳደር የሚችሉ (ራስ ገዝ) ኢንተርፕራይዞች እንዲፈጠሩ   የሚደግፍ በአዲስ አበባ ለሚኖሩ ነዋሪዎች በሙሉ በመንግስት ሀላፊነት ተሰጠው ቢሮ ነው፡፡ አገልገሎቱ በቢሮ ደረጃ በእንዳንዱ ክፍለከተማ ውስጥ ባሉት ወረዳዎች ይሰጣል፡፡ አሁን ባለው አሰራር 11 ክፍለ ከተማዎች እና 121 ወረዳዎች ይገገኛሉ፡፡

 

የቢሮው የተመሰረተበት ዋናዎ አላማው ብዙ ፤ ግዙፍና ትርፋማ ኢንተርፕራይዞችን ለስራፈላጊዎች እና ለስራ ፈጣሪዎች እንዴት አድርገው ፤ የት ቦታ እና ምን አይነት ድጋፍ ቢሰጥ ውጡታማ የሚሆኑበትን መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡. ይህ በመሆኑም የከተማው ታክስ ከፋይ ቅጥር እና ኢኮኖሚው እንዲያድግ በተያያዥም ንግድ ትስስሩ ማለትም የአምራች  እና የተቀባይ ትስስሩ እንዲበራከት ያደርገዋል፡፡ቢሮው የተቀላጠፈ አገልሎት ለመስጠት በማቀድ "የአንድ ማእከል አገልግሎት" በእያንዳንዱ ክፍለከተማ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ላይ እንዲተገበር አርጉዋል፡፡ ይህም በመሆኑ  ምዘናን በጠነቀ መልኩ ብዙ ቁጥር ያላቸው ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ እንዲስተናገዱ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡  "የአንድ ማእከል አገልግሎት" ዋና አላማ ኢንተርፕራይዝ ሲመመስረት አስፈላጊውን የምስክር ወረቀት የሚሰጡትን  መስራቤቶችን ሁሉ በአንድ ሲሰተም አንድ ላይ በማምጣት (በበይነመርብ) የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ነው፡፡

 

 

የሥራ አጥነት መታወቂያ ምዝገባ

ኢንተርፕራይዝ ለማመልከት

ነባር ኢንተርፕራይዝ ለማመልከት

ከአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም የገንዘብ ብድር ለማግኘት ማመልከት

የካፒታል ዕቃዎች እና ማሽነሪዎች ለማግኘት ማመልከት

መስሪያ ቦታ ለማግኘት ማመልከት

የገበያ ትስስር እንዲመቻች ማመልከት